ቀጥታ፡

አውስትራሊያ የዓለም ዋንጫውን በድል ጀምራለች

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ አውስትራሊያ ቱርኪዬን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ዛሬ ማለዳ በቢሲ ፕሌስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኔስትሮይ ኢራንኩንዳ በ27ኛው እና ኮነር ሜትካልፍ በ75ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

አውስትራሊያ በጨዋታው ብልጫ ቢወሰድባትም ያገኘቻቸውን የግብ እድሎች በሚገባ መጠቀሟ አሸናፊ አድርጋለች።

ቱርኪዬ በጨዋታው ላይ የወሰደችውን ወደ ጎል መቀየር ተስኗቷል።

ውጤቱን ተከትሎ አውስትራሊያ በምድብ አራት በሶስት ነጥብ ተመሳሳይ ነጥብ ባላት አሜሪካ በግብ ክፍያ ተበልጣ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች።

ከትናንት በስቲያ በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር አሜሪካ ፓራጓይን 4 ለ 1 ማሸነፏ የሚታወስ ነው።

የምድባቸውን የመጀመሪያ ጨዋታ ያሸነፉት አሜሪካ እና አውስትራሊያ በቀጣይ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

ቱርኪዬ ከፓራጓይ ሌላኛው የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም