ቀጥታ፡

የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና  ከኢትዮጵያ ቡና ጋር ወሳኝ ጨዋታ ያደርጋል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ)፦ ከኢትዮጵያና ማላዊ የወዳጅነት ጨዋታዎች መልስ፣ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ በ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር  ይመለሳል። 

ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ ቡና ከሲዳማ ቡና በአዲስ አባ ስታዲየም ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ ቡና በ46 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ሲዳማ ቡና በ61 ነጥብ ሊጉን እየመራ ነው።

በ34ኛ ሳምንት በሃዋሳ ከተማ 1 ለ 0 የተሸነፈው ኢትዮጵያ ቡና ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይጫወታል። 

በአንጻሩ ሲዳማ ቡና ካሸነፈ ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይበልጥ ይቃረባል።

ተከታዩ መቻል በቅዱስ ጊዮርጊስ ከተሸነፈ ሶስት ጨዋታዎች እየቀሩ የሊጉን ዋንጫ ማንሳቱን ያረጋግጣል። 

የቅዱስ ጊዮርጊስ እና መቻል ጨዋታ ከቀኑ 9 ሰዓት በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል።

የ16 ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ46 ነጥብ ስምትኛ ደረጃን ይዟል። መቻል በ53 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች ያሸነፈው ቅዱስ ጊዮርጊስ በድል ጉዞው ለመቀጠል ይፋለማል።

ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ያላገኘው መቻል በዋንጫ ፉክክሩ ላይ ለመቆየት ሶስት ነጥብ ማግኘት ይኖርበታል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድን ከድሬዳዋ ከተማ በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

የወቅቱ የሊጉ የዋንጫ አሸናፊ ኢትዮጵያ መድን በ43 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊጉ ጨዋታዎች ነጥብ ተጋርቷል።

ድሬዳዋ ከተማ በ35 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ስምንት የሊግ ጨዋታዎች ከድል ርቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር  እስከ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የሲዳማ ቡናው አቤል ያለው በ14 ጎሎች የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነቱን እየመራ ነው። የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ ናትናኤል ዳንኤል በ13 ግቦች ይከተላል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም