ስኮትላንድ ድል ቀንቷታል - ኢዜአ አማርኛ
ስኮትላንድ ድል ቀንቷታል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 7/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ የምድብ ሶስት ሁለተኛ መርሐ ግብር ስኮትላንድ ሀይቲን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
በቦስተን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆን ማጊን በ29ኛው ደቂቃ ጎሉን አስቆጥሯል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።
ግብ ያስቆጠረው ማጊን የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
ውጤቱን ተከትሎ ስኮትላንድ ምድብ ሶስትን በሶስት ነጥብ መምራት ጀምራለች።
በዚህ ምድብ ትናንት በተደረገው ጨዋታ ብራዚል እና ሞሮኮ አንድ አቻ ተለያይተዋል።
ሞሮኮ ከስኮትላንድ፣ ብራዚል ከሀይቲ በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ሁለተኛ ጨዋታዎች ናቸው።