ቀጥታ፡

በዓለም ዋንጫው ደቡብ ኮሪያ ድል ቀንቷታል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 5/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያ ከመመራት ተነስታ ቼክ ሪፐብሊክን 2 ለ 1 አሸንፋለች።

በጓድላሃራ ስታዲየም በተካሄደው እና ማለዳ ላይ በተጠናቀቀው የምድብ አንድ ጨዋታ ላዲስላቭ ክሬይቺ በ59ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ቼክ ሪፐብሊክ መምራት ችላለች።

ዋንግ ኢን-ቦም በ67ኛው እና ዮን-ግዩ ኦ በ80ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፏቸው ጎሎች ደቡብ ኮሪያን አሸናፊ አድርጓል።

ደቡብ ኮሪያ በመጨረሻ 30 ደቂቃ ያሳዩት እንቅስቃሴ ግቦቹን እንዲያስቆጥሩ አስችሏቸዋል።

በዚሁ ምድብ አንድ ትናንት በተደረገው የዓለም ዋንጫ የመክፈቻ ጨዋታ ሜክሲኮ ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 አሸንፋለች።

ሜክሲኮ ከደቡብ ኮሪያ እና ደቡብ አፍሪካ ከቼክ ሪፐብሊክ በቀጣይ በምድቡ የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም