ቀጥታ፡

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በባህር ዳር ይካሄዳል


አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር እሁድ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በባህር ዳር ከተማ ይከናወናል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ውድድሩን አስመልክቶ ዛሬ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ የሰጠ ሲሆን ለሩጫው አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን አመልክቷል።

በውድድሩ ላይ የግል ተወዳዳሪዎችን ጨምሮ ከስድስት ክለቦች የተውጣጡ 91 አትሌቶች ይሳተፋሉ።

ከ1ኛ እስከ 8ኛ ለሚወጡ አትሌቶች የገንዘብ ሽልማት እንደሚበረከትም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም