ቀጥታ፡

በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ ምህረት ተደረገላቸው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 4/2018 (ኢዜአ)፦ በሳዑዲ አረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ እንዲሰጣቸው መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያውያኑ ምህረት የተደረገላቸው ሚኒስቴሩ ሪያድ የሚገኘውን ሚሲዮን እና በጅዳ ያለውን ቆንስላ ጽህፈት ቤት በማስተባበር ባደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት መሆኑን አመልክቷል።

ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ መሆኑን ገልጿል።

መንግሥት ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረገ ይገኛል።

በዚሁ አጋጣሚ መንግሥት ሕብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሀሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ አገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ እያሳሰበ፤ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም