ቀጥታ፡

አንድ ሺህ ስምንት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል ገብቷል

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018 (ኢዜአ)፡-የአንድ ሺህ ስምንት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል መግባቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ገለጹ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ ዕለታዊ መግለጫ ሰጥቷል።


 

የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ በመግለጫቸው፤ የምርጫ ጣቢያዎች የውጤት ቆጠራ ተጠናቆ በምርጫ ክልሎች የማዳመር ስራ እየተከናወነ ነው።

በዚህም ከአንድ ምርጫ ክልል ውጭ በሁሉም የምርጫ ክልሎች የማዳመር ሥራ ተጠናቋል ብለዋል።

በዚህም የአንድ ሺህ ስምንት የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ቦርዱ የማረጋገጫ ማዕከል መግባቱን ገልጸዋል።

ከ501ዱ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች 446ቱ ወደ ማዕከል ደርሰዋል፣ ቀሪዎቹ የክልል ምክር ቤቶች ናቸው ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በመጠለያ ጣቢያዎችና በመከላከያ ካምፖች ድምፅ አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ውጤት የማዳመር ሥራ ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም