ቀጥታ፡

የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ዋዜማ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት የሚካሄደው 23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ነገ ይጀመራል።

በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ 48 ሀገራት ይሳተፋሉ።

ዓለም ዋንጫው ነገ በምድብ አንድ ሜክሲኮ ከደቡብ አፍሪካ ምሽት አራት ሰዓት ላይ በሜክሲኮ ሲቲ ስታዲየም በሚያደርጉት ጨዋታ ይጀመራል።

በዚሁ ምድብ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ላይ ኮሪያ ሪፐብሊክ ከቼክ ሪፐብሊክ በጓድላሃራ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ይጫወታሉ።

23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ እስከ ሐምሌ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም