ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ለሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 3/2018 (ኢዜአ)፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በሀገሪቱ ታሪክ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ መሪ በመሆናቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም ታላቅ ወንድሜ እና ውድ ወዳጄ ናሬንድራ ሞዲ፣ የዓለማችንን ትልቁን እና እጅግ ንቁ የሆነውን የዲሞክራሲ ማህበረሰብ ዘላቂ እምነት በማግኘት፣ ህንድን በራዕይ እና በቁርጠኝነት በተከታታይ ሶስት የዲሞክራሲያዊ የስልጣን ዘመናት በመምራት ላስመዘገቡት ታሪካዊ ስኬት የተሰማኝን ደስታ እገልጻለሁ ብለዋል።
የእርሳቸው አመራር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከድህነት ያወጣ፣ የዲጂታል ሕዝባዊ መሰረተ ልማትን በከፍተኛ ደረጃ ያስፋፋ እና ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ የመሰረተ ልማት እድገትን በማምጣት ፈጣን የኢኮኖሚ መነቃቃትን ያስገኘ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በተከታታይነት ለደቡቡ የዓለም ክፍል (Global South) ጠንካራ ድምጽ በመሆን አገልግለዋል ሲሉም ገልጸዋል።