ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ማላዊ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ አንድ አቻ ተለያይቷል።

ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አዴፖጁ ባባቱንቴ በ19ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ማላዊ መሪ ሆናለች።

ቢንያም በላይ በ42ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፋት ግብ ኢትዮጵያን አቻ አድርጓል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ሁለቱ ሀገራት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፍጹም ጥላሁን ጎል 1 ለ 0 ማሸነፉ የሚታወስ ነው።

ዋልያዎቹ ጨዋታዎቹን ያደረጉት፣ የፊፋ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች የጨዋታ ቀናትን (FIFA Window) በመጠቀም መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም