በሶስተኛው ዙር የጀመርናቸውን 13.4 ኪሜ የሚሸፍነውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን አፈፃፀም ገምግመናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ - ኢዜአ አማርኛ
በሶስተኛው ዙር የጀመርናቸውን 13.4 ኪሜ የሚሸፍነውን የኮሪደር ልማት ስራዎችን አፈፃፀም ገምግመናል-ከንቲባ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዛሬ ማለዳ በሶስተኛው ዙር የተጀመረውን 13.4 ኪሜ የሚሸፍን የኮሪደር ልማት ስራ አፈፃፀም መገምገማቸውን ገለጹ።
የኮሪደሮቹ ልማት በአምስት መስመሮች ተከፋፍለዉ እየተሰሩ ሲሆን እነርሱም፦
1- ከቦሌ መድሃኔዓለም እስከ ጎላጎል ( የቦሌ አትላስን መንገድ ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ)፣
2- ከጎላጎል እስከ እንግሊዝ ኤምባሲ (የቀበና መገናኛ መንገድን ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ) ፣
3- ከቦሌ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በሞኤኮ እስከ ቦሌ መገናኛ መንገድ ( የቦሌ አትላስን መንገድ ከቦሌ መገናኛ መንገድ ጋር የሚገናኝ)፣
4- ከኢምፔሪያል በአደይአበባ ስቴድዮም እስከ ሻላ መናፈሻ ፣
5-ከውሃ ልማት በአትላስ ያለውን እና ከአትላስ እስከ ቦሌ ሩዋንዳ ( የቦሌ አትላስ መንገድን ከመስቀል አደባባ መገናኛ መንገድ እና ከቦሌ አየርመንገድ ጋር የሚገናኝ) በከፍተኛ ደረጃ የመንገድ ትስስርን የሚያሰፋ፣ የንግድ ተቋማት ፣ ሰፋፊ የእግረኛ መንገድ፣ የሳይክል መንገድ እና ለትራንስፖርት አገልግሎት ምቹ እንዲሆኑ ተደርገው እየተገነቡም ናቸው።
በተጨማሪም በርካታ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን የግንባታውም ሂደትም በጥሩ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
በአደይአበባ ስታዲየም ዙሪያ አስቀድመው የተጀመሩ የኮሪደርና ሌሎች መሠረተ ልማት ግንባታዎች በፍጥነትና በጥራት እንዲከናወኑ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
ከኮሪደሩ በተጨማሪም ለብዙ ዘመናት ተረስቶ የኖረ፣ ከሕዝብ ተወስዶ በግለሰቦች ያለአግባብ ተወሮ ለብዙ ብልሽት ተዳርጎ የኖረውን ቦታ ለህዝብ አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ በመሰራት ላይ ይገኛል።
ፕሮጀክቶቹን እስከ ሰኔ ወር መጨረሻ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ለማዋል በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።