ቀጥታ፡

በክልሉ በሁሉም ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ይገባል

አዲስ አበባ፤ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦በከፍተኛ ትጋትና የአመራር ቁርጠኝነት የተመዘገቡ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ።

የሀረሪ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ከክልሉ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ጋር በቀጣይ ስራዎች ላይ የምክክር መድረክ አካሂዷል።


 

በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በክልሉ ባለፉት ጊዜያት በከፍተኛ ትጋትና የአመራር ቁርጠኝነት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልፀዋል።

በቀጣይም በልማት፣መልካም አስተዳደር ሰላም፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ገልጸዋል።

ለሕዝብ የገባነውን ቃል በተግባር ለማረጋገጥ አመራሩ በላቀ ቁርጠኝነት ሊሠራ ይገባልም ነው ያሉት።

እውነተኛ ዴሞክራሲን ከተጨባጭ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ስኬቶች ጋር በማጣመር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በተግባር የማረጋገጥ ስኬታችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።

በመሆኑም በከፍተኛ ትጋትና ቁርጠኝነት የተመዘገቡ የልማት፣የመልካም አስተዳደርና የሰላም ስኬቶችን አጠናክሮ ለማስቀጠል አመራሩ የአገልጋንነት መንፈስ በመላበስ ሊያገለግል ይገባል ብለዋል።

በተለይም የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፣የኑሮ ውድነቱን የማረጋጋት እና የሕግ የበላይነትን የማስከበር ሥራ ቅድሚያ ትኩረት በመስጠት የሚሰሩ ስራዎች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም