ቀጥታ፡

በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች ድምጽ እየሰጡ ነው

ደብረብርሃን፤ ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፡- በደብረ ብርሃን ከተማ በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምጽ እየሰጡ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የድምፅ አሰጣጥ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ማካሄዱ ይታወቃል።


 

ቦርዱ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በመደበኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ ሁኔታ ላልተሳተፉ ዜጎች ደግሞ የድምጽ መስጫ ቀን የሚያመቻች መሆኑ ይታወቃል።

በመሆኑም በሀገር ውስጥ በጊዜያዊ መጠለያዎችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን በማቋቋም ዜጎች ድምፅ እንዲሰጡ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል።

በዚሁ መሰረትም በደብረ ብርሃን  ከተማ በሶስት በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ወገኖች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በዛሬው እለት ከማለዳው ጀመሮ ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

በጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች የሚገኙ ዜጎችም ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ይበጀናል የሚሉትን ፓርቲ በነጻነት እየመረጡ መሆኑን ገልጸዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም