ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታዋን ታደርጋለች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታዋን ታደርጋለች
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2 /2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ አቻው ጋር ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል።
ጨዋታው ምሽት 12 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ይከናወናል።
ሁለቱ ሀገራት ግንቦት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ባደረጉት የመጀመሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ በፍጹም ጥላሁን ጎል 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ይህ ውጤት ኢትዮጵያ ከአምስት ዓመታት በኋላ በማላዊ ላይ ያስመዘገበችው ድል ነው።
ኢትዮጵያ እና ማላዊ ከቀናት በፊት የተደረገውን የወዳጅነት ጨዋታ ጨምሮ 15 ጊዜ ተገናኝተዋል።
ሁለቱም ቡድኖች በተመሳሳይ አምስት ጊዜ ሲያሸንፉ በቀሪ አምስት ጨዋታዎች አቻ ወጥተዋል።
ኢትዮጵያ በጨዋታዎቹ ላይ 17 ግቦችን ከመረብ ላይ ስታሳርፍ ማላዊ 14 ጎሎችን አስቆጥራለች።
ብሔራዊ ቡድኖቹ ከዛሬው ጨዋታ በፊት የመጨረሻ ልምምዳቸውን ትናንት በድሬዳዋ ስታዲየም አከናውነዋል።
የኢትዮጵያ ተጫዋቾች በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ዋልያዎቹ ጨዋታዎቹን እያደረጉ የሚገኙት፣ የፊፋ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች የጨዋታ ቀናትን (FIFA Window) በመጠቀም መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።