ቀጥታ፡

በካምፖች በመራጭነት የተመዘገቡ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 2/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ማካሄዱ ይታወቃል።

ቦርዱ በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 17 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት በመደበኛው ጠቅላላ ምርጫ በልዩ ሁኔታ ላልተሳተፉ ዜጎች የድምጽ መስጫ ቀን ያመቻቻል።


 

በመሆኑም በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችና በወታደራዊ ካምፖች ልዩ ጣቢያዎችን አቋቁሟል።

ይህም የካምፑ ነዋሪዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ እንዲሣተፉ በመራጭነት በመዘገበው መሠረት የሚካሄድ ነው።


 

በመሆኑም በካምፖች በመራጭነት የተመዘገቡ ዜጎች ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ድምጻቸውን እየሰጡ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም