ምክር ቤቱ የጉምሩክ ማሻሻያ እና የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጆችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል - ኢዜአ አማርኛ
ምክር ቤቱ የጉምሩክ ማሻሻያ እና የቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጆችን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/2018 (ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በ5ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ 24ኛ መደበኛ ስብሰባውን ነገ ያካሂዳል።
ምክር ቤቱ በዚሁ መደበኛ ስብሰባው የጉምሩክ አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ይመክራል።
በጉዳዩ ላይ የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮም አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቁልፍ መሠረተ ልማቶች የሳይበር ደህንነት ረቂቅ አዋጅ ላይ ያዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሐሳብ መርምሮ እንደሚያጸድቅም ምክር ቤቱ አመልክቷል።