የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከዛምቢያ ጋር ጨዋታ የሚያደርግባቸው ቀናት ታውቀዋል - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከዛምቢያ ጋር ጨዋታ የሚያደርግባቸው ቀናት ታውቀዋል
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 1/ 2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዓለም ዋንጫ ማጣርያ የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ጨዋታዋን ከዛምቢያ ጋር ሰኔ 27 እና ሐምሌ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
በዚሁ መሰረት የመጀመሪያው ጨዋታ ዛምቢያ ላይ፣ የመልሱ ጨዋታ በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ኢትዮጵያ ብሩንዲን፣ ዛምቢያ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን በደርሶ መልስ ውጤት አሸንፈዋል።
ኢትዮጵያ በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ዓለም ዋንጫ ትሳተፋለች።
10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።
በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። በዓለም ዋንጫው አፍሪካ ሞሮኮን ጨምሮ በአምስት ሀገራት ትወከላለች። ቀሪ አራት ሀገራት በማጣሪያ ጨዋታዎች ይለያሉ።