ቀጥታ፡

የአረንጓዴ ዐሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሮች ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል

ጋምቤላ፤ ግንቦት 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአረንጓዴ ዐሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሐ-ግብሮች የፈጠሩትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስኬታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የጋምቤላ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።


 

በክልሉ የተተገበሩት የአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብሮች ለአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስኬታማነት ምቹ ሁኔታ ፈጥረዋል

ጋምቤላ፤ግንቦት 30/2018 (ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል የአረንጓዴ አሻራ እና የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብሮች የፈጠሩትን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም፣ በአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ረገድ ስኬታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ የተሸረሸሩ መሬቶችን ለማገገም እና የደን ሽፋንን ለማሳደግ ታስቦ እየተካሄደ ያለ መጠነ-ሰፊ ንቅናቄ ነው።

በሌላ በኩል፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የምግብና ሥነ-ምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የእንስሳት፣ የዶሮ፣ የንብ፣ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ ምርታማነትን በየቤተሰቡ ደረጃ ለማሳደግ ያለመ ነው።

እነዚህ ሁለቱ መርሃ-ግብሮች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፉ በመሆናቸው፣ በአንድ በኩል አካባቢን ሲጠብቁ በሌላ በኩል ደግሞ ለተቀናጀ የግብርና ልማት መሳካት ትልቅ መሠረት ጥለዋል።

በጋምቤላ ክልልም በሁለቱ መርሃግብሮች የተከናወኑት ተግባራት ውጤት እያስገኙ ነው።

የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንድሮው ቱት ለኢዜአ እንደገለጹት የአረንጓዴ አሸራና የሌማት ትሩፋት መርሃግብሮች የፈጠሯቸውን ምቹ አጋጣሚ በመጠቀም በክልሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ስኬታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው።

ቀደም ሲል ለፍጆታ ብቻ ይመረት የነበረው አትክልት አሁን ላይ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ሐባብና ብርቱካንን ጨምሮ ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች በአርሶ አደሮችና በባለሃብቶች በስፋት እየተመረቱ ለገበያ እየቀረቡ ነው ብለዋል።

በተለይም በማጃንግ ዞን በጎደሬና በመንጌሽ ወረዳዎች አቮካዶና ሙዝን ጨምሮ ሌሎች የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ወደ አዲስ አበባና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች ለገበያ በስፋት እየቀረቡ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በክልሉ በዘንድሮው ክረምትም ከአረንጓዴ አሻራ ልማቱ ጋር በማቀናጀት አቮካዶን ጨምሮ ከ8 ሚሊዮን በላይ የፍራፍሬና ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለቸው ችግኞችን ለመትከል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

በቢሮው የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ ፕሮግራም አስተባበሪ አቶ ሀብታሙ ገዳሙ እንዳሉት የምግብ ስርዓት ማጠናከሪያ መረሃ ግብር እንደ ሀገር የግብርናውን ዘርፍ ለማገዝ ከተቀረጹት ፕሮግራሞች መካከል አንዱ ነው።

በፕሮግራሙ እየተሰሩ ከሚገኙት የእሴት ሰንሰለት ሰብሎች መካከል አቮካዶ፣ ስንዴ፣ በቆሎና ሌሎችም እንደሚገኙበት አስተባበሪው ገልጸዋል።

በዘርፉ ልማት ከተሰማሩት አርሶ አደሮች መካከል የጎደሬ ወረዳ ጌለሻ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ሉቃስ ጎርሾ በሰጡት አትያየት አካባቢው አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ ለሁሉም የግብርና ልማት አመች ነው።

እናም ሙዝ፣ አቮካዶና ሌሎችንም የሰብል እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬዎችን በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው በገበያ ትስስር በኩልም የመንግስት እገዛ እንሚሹ ገልጸዋል።

ባለፉት ዓመታት በሙዝ ልማት በስፋት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆኑን የገለጸው ደግሞ የዚሁ ቀበሌ ነዋር ወጣት ሮቤል ሮኬት ነው።

በአሁኑ ወቅት ሰባት ሄክታር የሚደርስ ሙዝ በማልማት ምርቱን ወደ አዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች በመሸጥ ተጠቃሚ መሆኑን ጠቁመው የገበያ ትስስሩ ሊጠናከር ይገበል ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም