የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በጅግጅጋ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በጅግጅጋ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል
ጅግጅጋ፤ ግንቦት 29/2018(ኢዜአ)፦ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ እና የክልል ርዕሰ መስተዳድሮችና የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ከንቲባዎች ተሳትፈዋል።
በጉብኝቱም የጅግጅጋ ከተማ የኮሪደር ልማትን፣ የሶማሌ ክልል ፖሊስ ሆስፒታል ግንባታ ሂደትን፣ ሰይድ መሀመድ አብዲሌ ሀሰን መታሰቢያ ፓርክ እና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ያካተተ ነው።
የክልሉ ፖሊስ ሆስፒታል ግንባታን በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
የኮሪደር ልማት ሥራውም የከተማዋን ገጽታ ለመቀየርና የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑ ተመልክቷል።
ከዚህም ባለፈ ለህብረተሰቡ ቀልጣፋና የተቀናጀ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የብልጽግና ፓርቲ የሶማሌ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሕንፃ ግንባታ ክልሉ መልካም የልማት እንቅስቃሴ ላይ መሆኑን ያመላክታል ተብሏል።