ዋልያዎቹ ድል ቀንቷቸዋል - ኢዜአ አማርኛ
ዋልያዎቹ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 29/2018 (ኢዜአ)፦ በዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ ማላዊን 1 ለ 0 አሸንፋለች።
ማምሻውን በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፍጹም ጥላሁን ጨዋታው በተጀመረ በአንደኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ የሚባል ፉክክር ተደርጎበታል።
ብሔራዊ ቡድኖቹ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታቸውን ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ያደርጋሉ።
ኢትዮጵያ ጨዋታውን የምታደርገው፣ የፊፋ ዓለም አቀፍ የብሔራዊ ቡድኖች የጨዋታ ቀናትን (FIFA Window) በመጠቀም መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።