ቀጥታ፡

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጉዳያችንን ባጠረ ጊዜ መፈጸም አስችሎናል - ተገልጋዮች

ወላይታ ሶዶ፤ ግንቦት 29/2018(ኢዜአ)፦ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጉዳያቸውን ባጠረ ጊዜ መፈጸም እንዳስቻላቸው በወላይታ ሶዶ መሶብ የአንድ ማዕከል ተገልጋዮች ተናገሩ።

በወላይታ ሶዶ ለኢዜአ አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ተገልጋዮች መካከል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ለማውጣት ወደ ማዕከሉ የመጡት አቶ ተስፋዬ ዳና አገልግሎቱን በቅርበት በማግኘታቸው ጊዜ እና ገንዘብ እንደቆጠበላቸው ተናግረዋል።

የአገልግሎት አሰጣጡ ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ከዚህ ቀደም ይስተዋል የነበረን መጉላላት ያስቀረ መሆኑን ጠቅሰዋል።


 

አገልግሎቱ ፓስፖርት ለማውጣት ወደ ሐዋሳ በመሄድ ለበርካታ ቀናት የነበረውን መዘግየት እንዳስቀረለት የተናገረው ደግሞ የወላይታ ሶዶ ከተማ ነዋሪ ወጣት በላቸው ዘውዴ ነው።

መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በፍጥነት በመስተናገድ ጊዜ፣ ጉልበትና ወጪን መቀነስ በመቻሉ መደሰቱን ጠቅሶ አገልግሎቱ ይበልጥ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አመልክቷል።


 

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ኃላፊ እና የወላይታ ሶዶ የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ደመላሽ ታደሰ በበኩላቸው በማዕከሉ 4 የፌዴራልና 5 የክልል ተቋማት 32 የተለያዩ አገልግሎቶችን እየሰጡ መሆኑን ገልጸዋል።

ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠት መቻሉን ጠቁመዋል።

በቀጣይ አገልግሎቱን ይበልጥ በማሻሻል የህዝብ ቅ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም