ቀጥታ፡

በሐረሪ ክልል ከ38 ሺ 300 በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ወስደዋል- የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ከ38 ሺ 300 በላይ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መውሰዳቸውን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገለጹ።

የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም በሰጡት መግለጫ፤ የኮደርስ ሥልጠናው የዜጎችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎት በማዳበር ረገድ እንደ አገር የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለማሳለጥ ትልቅ እገዛ አለው ብለዋል።

እስካሁን በኢኒሼቲቩ በተከናወነው ስራ በክልል ደረጃ ስልጠናውን ካጠናቀቁ ወጣቶች መካከል 27 ሺህ 574 የሚሆኑት የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል።

በመርሐ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ፣ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ለማፍራት የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል።

ሥልጠናው ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርግ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው፤ ዕድሉን ያላገኙ ወጣቶች በቀጣይ ተመዝግበው እንዲሰለጥኑም ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም