በጠቅላላ ምርጫው የታየውን አንድነት ለሀገር ልማት ማዋል ይገባል – ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በጠቅላላ ምርጫው የታየውን አንድነት ለሀገር ልማት ማዋል ይገባል – ነዋሪዎች
ሸገር ፤ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ)፦ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየውን አንድነት በሀገር ልማት ላይም መድገም እንደሚገባ የሸገር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ በሸገር ከተማ የቡራዩ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች መካከል፤ ሃደ ሲንቄ ካባ በየና ህዝቡ በምርጫው ላይ ተሳትፎ ለሚፈልገው ፓርቲ ድምጽ መስጠቱ ለሀገር ልማት መረጋገጥና ቀጣይነት ትልቅ ዋስትና ነው።
በመሆኑም በምርጫው የታየውን የአንድነት መንፈስ ቀጣይነት ላለው ልማትና ሀገር ግንባታ መድገም እንደሚገባ ገልጸዋል።
ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ኢላላ ዲሮ በበኩላቸው፤ በምርጫው ወቅት የታየውን ጠንካራ ተሳትፎ ወደ ልማት በማዞር ሀገራችንን ማሳደግ ይጠበቅብናል ብለዋል።
በዘንድሮ ጠቅላላ ምርጫ እጅግ በርካታ ህዝብ መሳተፉን የገለጹት አባ ገዳ ቶሊ ኤግዱ፤ ይህንን የጋራ ተሳትፎ ለሀገር ሰላምና ግንባታ ልንጠቀምበት ይገባል ነው ያሉት።
ወጣት ታምሩ ደባ በበኩሉ፤ ምርጫው የነቃ የህዝብ ተሳትፎ የታየበት መሆኑንና በምርጫው የታየው ታላቅ ተነሳሽነት ለሀገር ግንባታ ሊውል ይገባል ሲል ተናግሯል።