ሴቶች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ አድርገዋል - ኢዜአ አማርኛ
ሴቶች በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ አድርገዋል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ)፦ሴቶች ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ ማድረጋቸውን የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ገለፀ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የነበረውን አጠቃላይ የድምጽ አሰጣጥ ሂደትን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር ገነት ስዩም በመግለጫቸው፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ፌዴሬሽኑ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል።
በዚህም የፌዴሬሽኑ አባላት ገለልተኝነታቸው ጠብቀው የታዛቢነት ሚናቸውን በአግባቡ እንደተወጡ ተናግረዋል።
ፌዴሬሽኑ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አጠቃላይ ከ14 ሺህ በላይ ታዛቢዎችን በማሰማራት 25 ሺህ 384 የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የመታዘብ ስራ ማከናወኑን ጠቁመዋል።
የሴቶች ተሳተፎ ከቀደሙት የምርጫ ጊዚያቶች ሲነፃፀር መሻሻል ማሳየቱ ገልጸው፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በመራጭነትና በታዛቢነት አበረታች ተሳትፎ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።