የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላላ ምርጫው ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በሁሉም የልማት መስኮች ለመድገም ተዘጋጅተዋል - ኢዜአ አማርኛ
የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላላ ምርጫው ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በሁሉም የልማት መስኮች ለመድገም ተዘጋጅተዋል
ሆሳዕና፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦የሆሳዕና ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላላ ምርጫው ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በቀጣይ በሁሉም የልማት ሥራዎች ላይ በድጋሚ ለማረጋገጥ መዘጋጀታቸውን ገለጹ።
በሆሳዕና ከተማ የሴች ዱና ቀበሌ ነዋሪዋ ወይዘሮ እንዳሻሽ ፀጋዬ እንደገለጹት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ ይበጀናል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ ሰጥተዋል።
በምርጫ ወቅት ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም በሀገር ልማት ላይ በመድገም የተጀመረውን ሀገራዊ ልማት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል።
በከተማው በሊች አምባ ቀበሌ የሚኖሩት አቶ ሀብቴ አስራት በሰጡት አስተያየት፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመሳተፍ ይበጀኛል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ሰጥተዋል።
በምርጫው ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በቀጣይም በልማት እንደሚደግሙት ገልፀዋል።
በሆሳዕና ከተማ ሄጦ ቀበሌ ነዋሪዋ ዓለምፀሐይ ደስታ፤ በጠቅላላ ምርጫው በመሳተፍ ድምጻቸውን ለሚፈልጉት ፓርቲ በመስጠት ታሪካዊ አሻራቸውን ማሳረፋቸውን ተናግረዋል።
በቀጣይም የልማት እና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ተጠቅመው ለፈለጉት ፓርቲ ድምጻቸውን በመስጠት ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እንደተወጡ የገለጹት ደግሞ በከተማው የአራዳ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ደበበ ባሻ ናቸው።
በቀጣይም ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ልማት መጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።