ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ - ኢዜአ አማርኛ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 28/2018 (ኢዜአ) ፦ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር ዓሊ አብዶ ኅልፈት የተሰማቸውን ኀዘን ገለጹ፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት የኀዘን መግለጫ፣ በቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ አምባሳደር አሊ አብዶ ህልፈተ ህይወት ጥልቅ ኀዘን ተሰምቶኛል ብለዋል።
አምባሳደር ዓሊ አብዶ 27ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ በመሆን እንዲሁም በሱዳን እና በናይጄሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር በመሆን ሀገራቸውን ያገለገሉ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ለወዳጆቻቸው እና ለመላው ሕዝብ መጽናናትን በመመኘት ፈጣሪ ነብሳቸውን በአጸደ ገነት ያኑር ብለዋል።