ወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ወላይታ ድቻ እና ነገሌ አርሲ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የተካሄደው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው።
ውጤቱን ተከትሎ ወላይታ ድቻ በ44 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት የሊግ ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።
ነገሌ አርሲ በ53 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች ከድል ርቋል።
ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ ጨዋታ፣ በወቅቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወደ ዛሬ መዘዋወሩ የሚታወስ ነው።