በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመጠጥ ውሃ ችግርን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመጠጥ ውሃ ችግርን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው
ሰቆጣ፤ ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር የመጠጥ ውሃ ችግርን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ የልማት ስራዎች በስፋት እየተከናወኑ መሆኑን የአስተዳደሩ ውሃና ኢነርጅ መምሪያ አስታወቀ።
በመምሪያው የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ ክትትል ባለሞያ ታደሰ አዳነ፤ በመንግስት በተሰጠው ልዩ ትኩረት አካባቢው የውሃ ሃብት አማራጮችን በማልማት ጥቅም ላይ እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
በዚሁ መሰረትም በበጀት ዓመቱ 56 አዲስ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶቸን ለመገንባት ታቅዶ እስካሁን 29 የሚሆኑት ግንባታቸው ተጠናቆ ለአገልግሎት በቅተዋል ብለዋል።
በእቅዱ መሰረት ሌሎች የግንባታ ስራዎችንም በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የተገነቡ የውሃ ፕሮጀክቶች የተሟላና ዘላቂ አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻልም ህብረተሰቡን ያሳተፈ የአጠቃቀምና አስተዳደር አገልግሎት እየተከናወነ መሆኑንም አንስተዋል።
የመጠጥ ውሃ ችግርን በዘላቂነት መፍታት የሚያስችሉ የልማት ስራዎች በአስተዳደሩ በስፋት እየተከናወኑ መሆኑንና ተጠናከረው የሚቀጥሉ መሆኑን ገልጸዋል።