በበጀት ዓመቱ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራትን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል - ኢዜአ አማርኛ
በበጀት ዓመቱ የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራትን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል
አዲስ አበባ፤ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ)፦በ2018 በጀት ዓመት የህዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ተግባራትን ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል ሲሉ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለጹ።
በሀረሪ ክልል በ2018 በጀት ዓመት ቀሪ ጊዜያት በሚከናወኑ ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጓል።
በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት፥ የበጀት ዓመቱ ቀጣይ እቅዶችን በስኬት ለማጠናቀቅ በትኩረት ይሰራል።
በመሆኑም ተቋማት የማህበረሰቡን የመልካም አስተዳደርና ልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የጀመሯቸውን ተግባራት በቀሪ ጊዜያት ለማጠናቀቅ በትኩረት ሊሰሩ እንደሚገባ ገልፀዋል።
በተለይም በቱሪዝም ልማት፣የትምህርትና የጤና አገልግሎት ጥራትና ተደራሽነትና በኮሪደር ልማት ላይ የተመዘገቡ አበረታች ውጤቶችን አጠናክሮ ማስቀጠል ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ገልፀዋል።
የሌማት ትሩፋት እና የከተማ ግብርና ስራዎችን በማጠናከር የግብርና ምርትና ምርታማነትን የማሳደጉ ስራም በበጀት ዓመቱ በልዩ ትኩረት ተጠናክረው የሚቀጥሉ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።
ለዜጎች የስራ ዕድል ፈጠራ ትኩረት በመስጠት የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው እንዲጎለብት ለማድረግ በቀጣይ ርብርብ እንደሚደረግም ገልፀዋል።