ቀጥታ፡

የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር

 

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 27/2018 (ኢዜአ)፦  በዝናብ ምክንያት የተራዘመው የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት ጨዋታ ዛሬ ይካሄዳል።

ጨዋታው ከቀኑ 9  ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይከናወናል።

ወላይታ ድቻ በሊጉ ካደረጋቸው 33 ጨዋታዎች መካከል በዘጠኙ ድል ሲቀናው ስምንት ጊዜ ሽንፈት አስተናግዷል። በቀሪ 16 ጨዋታዎች ላይ አቻ ተለያይቷል።

በ33ቱ ጨዋታዎች ላይ 32 ግቦችን ከመረብ ላይ ሲያሳርፍ 29 ግቦችን አስተናግዷል።

ወላይታ ድቻ በ43 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል።

ተጋጣሚ ነገሌ አርሲ በበኩሉ 33 ጨዋታዎችን አድርጎ በ13ቱ ሲያሸንፍ በሰባቱ ተሸንፏል። 13 ጊዜ ደግሞ ነጥብ ተጋርቷል።

32 ግቦችን ሲያስቆጥር 25 ጎሎች ተቆጥረውበታል።  ነገሌ አርሲ በ52 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ወላይታ ድቻ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይቷል።  ነገሌ አርሲም ካለፉት ሁለት ጨዋታዎች ሶስት ነጥብ ማግኘት አልቻለም።

ጨዋታው ሁለቱ ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ የሚያደርጉት ነው።

ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊካሄድ የነበረው የወላይታ ድቻ እና የነገሌ አርሲ ጨዋታ፣ በወቅቱ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት ወደ ዛሬ መዛወሩ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም