የምርጫ ሂደቱ ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበት ነው - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት - ኢዜአ አማርኛ
የምርጫ ሂደቱ ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበት ነው - የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት
አሶሳ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የምርጫ ሂደቱ ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ አብዱሰላም ሸንገል፤ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም ምርጫው የዜጎች የነቃ ተሳትፎ ጎልቶ የታየበትና በነፃነት ድምፅ የሰጡበት ታሪካዊ ምርጫ መሆኑን ተናግረዋል።
በድምጽ መስጫው ቀን ህብረተሰቡ ከማለዳ ጀምሮ እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ድምጹን ለመስጠት ያሳየው ተነሳሽነትም የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎችም ለምርጫው ያደረጉት ቅድመ ዝግጅት የሚደነቅ እንደነበር አስታውሰው የምርጫ ሂደቱ ለጠንካራ ሀገረ መንግስትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ የዜጎች የነቃ ተሳትፎ የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
በምርጫ ሂደቱ የፀጥታ አካላት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት እና የምርጫ አስፈጻሚዎች የነበራቸው ቅንጅታዊ አሰራር የሚያስመሰግን ነበር ብለዋል።
ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ እስከ ምሽት ድምፃቸውን በመስጠት የነበራቸው ጠንካራ ተሳትፎም ለአፍሪካ የምርጫ ሂደት በጥሩ ማሳያነት የሚጠቀስ መሆኑን ታዛቢ ቡድኑ አመላክቷል።