ቀጥታ፡

አዲስ አበባ የኖርዲክ-አፍሪካ ኢቪ ሰሚትን በብቃት ለማስተናገድ ዝግጁ ናት -ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ አዲስ አበባ የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚትን በብቃት ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኗን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንሰን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ከንቲባዋ በመጪው መስከረም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኖርዲክ - አፍሪካ ኢቪ ሰሚት (Nordic Africa EV Summit) በጋራ በሚሰሩ ጉዳዮች ላይ ከአምባሳደሩ ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።

ከተማዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ኩነቶችን የማስተናገድና በብቃት የመወጣት ልምድ ያካበተችና ተመራጭ እየሆነች የመጣች በመሆኗ፣ ይህንንም ጉባኤ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ታሳካዋለች ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም