በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ይበጀናል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት ድምጽ መስጠታቸውን ተመልክቻለሁ -የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን - ኢዜአ አማርኛ
በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ይበጀናል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት ድምጽ መስጠታቸውን ተመልክቻለሁ -የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦ በሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ይበጀናል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት ድምጽ መስጠታቸውን መታዘቡን የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ገለጸ።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌዴሬሽን ግንቦት 24/ 2018 ዓም የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት በሚመለከት ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ተወካይ አሌክሳንደር ንጉሴ እንዳሉት፤ ፌዴሬሽኑ በምርጫው እንደሀገር ወጣቶችን በታዛቢነትና በመራጮች ትምህርት መስጠት ሂደት በማሳተፍ ሀላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን ገልፀዋል።
ፌዴሬሽኑ በተሰጠው የታዛቢነት ኃላፊነት መሰረት ምርጫውን በነፃነት፣ በገልተኝነት በሙያዊ ስነምግባርና በከፍተኛ ሀላፊነት ተከታትሎ መታዘብ መቻሉን ገልፀዋል።
በሂደቱ የፌዴሬሽኑ ታዛቢዎች ከተለያዩ የፖለቲካ ፖርቲዎች ተወካዮች፣ ከሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በቅንጅት በመስራት ሀላፊነቱን በብቃት መወጣት መቻሉን ገልፀዋል።
በዚህም በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች ይበጀኛል ላሉት የፖለቲካ ፓርቲ በነጻነት ድምጽ መስጠታቸውን መታዘቡን ገልጿል።