ቀጥታ፡

አንዶኒ ኢራኦላ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ)፦አንዶኒ ኢራኦላ እስከ ሰኔ 2028 (እ.አ.አ) የሚቆይ የሁለት አመት ውል በመፈረም አዲሱ የሊቨርፑል አሰልጣኝ ሆኗል።

የቀድሞውን አሰልጣኝ አርነ ስሎትን በመተካት የሊቨርፑልን የአሰልጣኝነት መንበር የሚረከበው ኢራኦላ፤ በያዝነው ሳምንት ውስጥ በይፋ ለደጋፊዎችና ለሚዲያ እንደሚተዋወቅ የስፖርት ጋዜጠኛው ፋብሪዚዮ ሮማኖ ገልጿል።

የ43 ዓመቱ አሰልጣኝ ቦርንማውዝን በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሊጉ 6ኛ ደረጃን ይዞ እንዲያጠናቅቅ በማድረግ ለዩሮፓ ሊግ ተሳትፎ ማብቃት ችሏል።

አሰልጣኝ አንዶኒ ኢራኦላ ከእሱ ጋር አብረው የሚሰሩትን ፓብሎ ዴ ላ ቶሬ፣ ቶሚ ኤልፊክ፣ ሻውን ኩፐር እና ቶም ዌበርን ያካተተ የአሰልጣኞች ቡድን ወደ አንፊልድ ይዞ እንደሚመጣ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም