ቀጥታ፡

በኢትዮጵያ የተካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የተመራበት መንገድ የሚደነቅ ነው 

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ለመምራት ያደረገው ዝግጅት እና ምርጫውን ያስፈፀመበት አቅም የሚደነቅ መሆኑን የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የምርጫ ታዛቢዎች ቡድን መሪዎች ገልጸዋል።

የአፍሪካ ኅብረት እና የኢጋድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ታዛቢዎች ቡድን አጠቃላይ የምርጫው ሂደት ዙሪያ ያጠናቀሩትን የመጀመሪያ የግምገማ ውጤት የተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ምርጫ ቦርድ ያሳየው ገለልተኝነት፣ የቴክኖሎጂ ዝግጅቱ፣ አካታችነቱ እና የምርጫው አስተዳደር ጠንካራ እንደነበረ አንስተዋል።

እጩ ተመራጮች እና መራጮች በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በቴክኖሎጂ የታገዘ ምዝገባ ማድረጋቸውን እንደታዘቡም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም