ቀጥታ፡

የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን ማምረት ስንችል ነው

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018(ኢዜአ)፦የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዐት የሚረጋገጠው በጥራት፣ በዓይነት እና በብዛት የኢንዱስትሪ ምርቶችን በራስ ዕውቀት፣ በራስ ክህሎት እና በራስ ቴክኖሎጂ ማምረት ስንችል ነው ብለዋል፡፡

መንግሥትም በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የታለመውን ዘላቂ ዕድገት እና ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎችን ማሻሻሉን፡ አሠራሮችን መዘርጋቱን እና ማበረታቻዎችን ማድረጉን ገልጸዋል።

የዚህ ሪፎርም አካል የሆነው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም ፍሬው በግልጽ እየታየ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም