ቀጥታ፡

የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ኢትዮጵያ ያከናወነችውን የሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ሒደትን አደነቁ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2018(ኢዜአ)፦ የአውሮፓ ኅብረት እና አጋር ሀገራት ኢትዮጵያ ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ያካሄደችውን ሰባተኛውን ጠቅላላ ምርጫ ሂደት አድንቀዋል፡፡

መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ የኅብረቱ አባል ሀገራትና በኢትዮጵያ የካናዳ፣ የኖርዌይ እና ስዊዘርላንድ ኤምባሲዎች ምርጫውን አስመልክተው የጋራ መግለጫ አውጥተዋል፡፡

በመግለጫቸውም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ አስፈጻሚዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ እጩዎችና የሲቪል ተቋማት ጠቅላላ ምርጫው በስኬት እንዲካሄድ ያደረጉትን አስተዋጽኦም እንዲሁ አድንቀዋል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) በምርጫው ላይ ለነበራቸው የታዛቢነት ሚና እውቅና መስጠታቸውንም ሀገራቱ አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም