ቀጥታ፡

የምርጫ ንቁ ተሳትፏችንን በልማት ለመድገም ተዘጋጅተናል- የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች 

ሃዋሳ ፤ግንቦት 25/2018 (ኢዜአ)፦በምርጫ ወቅት ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በልማት ለመድገም መዘጋጀታቸውን የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡

በከተማዋ የተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት ተለጥፎ ለህዝብ ይፋ የተደረገ ሲሆን ህብረተሰቡም ውጤቶቹን እየተመለከተ ነው። 

ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶችን ሲመለከቱ ኢዜአ ያነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች በምርጫ ወቅት ያሳዩትን ንቁ ተሳትፎ በቀጣይ በልማት ሥራ እንደሚደግሙ ተናግረዋል።    

ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል በከተማው የለኩ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ታከለ ሱንደዶ እና የዳቶ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ቶማስ ፈልታሞ፤ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ላይ በንቃት መሳተፋቸው እንደሚያኮራቸው ገልጸዋል።

አቶ ቶማስ ጨሬ እና አቶ ከበደ ዮናስ በበኩላቸው፤ ህዝብ የስልጣን ባለቤት መሆኑን ባረጋገጠበት ጠቅላላ ምርጫ ያሳዩትን ተሳትፎ በልማት እንደሚደግሙ አረጋግጠዋል።   

በሃዋሳ ምርጫ ክልል በ08 ምርጫ ጣቢያዎች ትናንት ድምጽ የተሰጠ ሲሆን የድምጽ ቆጠራ ተጠናቆ የተለጠፉ ጊዜያዊ ውጤቶችን ህዝቡ እየተመለከተ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም