በጠቅላላ ምርጫው የታየው የህዝብ ተሳትፎ የልማት መነሳሳትን የሚያጠናክር ነው -የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች - ኢዜአ አማርኛ
በጠቅላላ ምርጫው የታየው የህዝብ ተሳትፎ የልማት መነሳሳትን የሚያጠናክር ነው -የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች
አዳማ ፤ግንቦት 25/2018 (ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የታየው የህዝብ ተሳትፎ የልማት መነሳሳትን እንደሚያጠናክር የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ።
አስተያየት ሰጪዎቹ እንደተናገሩት፤ በምርጫው የታየው ተሳትፎ ለልማት እና ለእድገት በጎ አስተዋጽኦ ያለው ነው።
ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ሲስተር ዓለም ጀማል እንዳሉት፤ በጠቅላላ ምርጫው የታየው የህዝብ ተሳትፎ በትብብር እና በህብረት ሀገራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሻገር እንደሚቻል ያሳየ ነው።
በአዳማ ከተማ የልማት እና የመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲቀጥሉ የበኩላቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጪ አቶ ንጉሴ ኦብሴ፤ ህዝቡ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሌሊት ብርድና በረጃጅም ሰልፎች ሳይበገር ያሳየው ጽናትና ቁርጠኝነት፣ ለልማት ያለውን መነሳሳት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች እንዲቀጥሉ የሚጠበቅብኝን እወጣለሁ ብለዋል።
አቶ ጌታቸው ወርቅነህ በበኩላቸው በምርጫው የታየው የህዝብ ተሳትፎ ህዝቡ ለሰላምና ለልማት ያለውን ተነሳሽነት በግልጽ ያሳየ መሆኑን ተናግረዋል።
ወደ ፊትም አንድነታችንን በማጠናከር በልማት ስራዎች ላይ መረባረብ አለብን ብለዋል።