ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት መቆጠብ ይገባል-ቦርዱ - ኢዜአ አማርኛ
ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት መቆጠብ ይገባል-ቦርዱ
አዲስ አበባ፤ግንቦት 25/2018 (ኢዜአ)፦የምርጫ ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት መቆጠብ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሳሰበ።
ቦርዱ በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ በትዕግሥት እንድትጠባበቁ ሲል ጠይቋል።
ቦርዱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፥ በትላንትናው ዕለት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በከፍተኛ ንቃትና ትዕግሥት ድምፅ ለሰጡ መራጮችም ምስጋና አቅርቧል።
በዚህም በምርጫ ሕጉ መሠረት ውጤት በቦርዱ ይፋ እስከሚሆን ድረስ በትዕግሥት መጠባበቅ እንደሚገባ ገልጾ፥ከሌሎች ከማንኛውም ምንጮች የሚወጡ መረጃዎችን ከማሠራጨት እንድትቆጠቡ ሲል ቦርዱ አሳውቋል፡፡