የአንድ ድምፅን ዋጋ የተረዱ የአዲስ አበባ ከተማ መራጮች - ኢዜአ አማርኛ
የአንድ ድምፅን ዋጋ የተረዱ የአዲስ አበባ ከተማ መራጮች
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ የአንድ ድምፅን ዋጋ የተረዱ የአዲስ አበባ ከተማ መራጮች በምሽቱ ብርድ ሳይገደቡ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ መራዘሙን መግለጹ ዘሙ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት ድምጽ የመስጠት ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የአዲስ አበባ አካባቢዎች ነዋሪዎች የምሽቱ ብርድ ሳይገድባቸው በተራዘመው የድምጽ መስጫ ሰዓት ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ።
የአንድ ድምፅ ዋጋን በመረዳት ሳንመርጥ ወደ ቤታችን አንመለስም ያሉት ድምጽ ሰጪዎቹ ድምፃቸውን ለሚፈልጉት ፓርቲ እየሰጡ ናቸው።