የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ምሽቱ ሳያግዳቸው የዜግነት መብታቸውን ድምጽ በመስጠት እያረጋገጡ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ምሽቱ ሳያግዳቸው የዜግነት መብታቸውን ድምጽ በመስጠት እያረጋገጡ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ምሽቱ ሳያግዳቸው የዜግነት መብታቸውን ድምጽ በመስጠት እያረጋገጡ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ማራዘሙ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት የአርባ ምንጭ ከተማ ነዋሪዎች ምሽቱ ሳያግዳቸው በተራዘመው የድምጽ መስጫ ሰዓት መብታቸውን ለመጠቀም ድምጽ እየሰጡ ይገኛሉ።