ቀጥታ፡

ዋልያዎቹ ዝግጅታቸውን ጀምረዋል

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር ለሚያከናውናቸው የወዳጅነት ጨዋታዎች ዝግጅቱን ዛሬ ጀምሯል።

አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳሕሌ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ካደረጉ በኋላ ዛሬ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ የመጀመሪያ ልምምዳቸውን አድርገዋል።

መስፍን ታፈሰ በጉዳት ምክንያት ከስብስቡ ውጪ በመሆኑ 22 ተጫዋቾች በልምምዱ መርሐ ግብር ላይ መገኘታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።




ሙሴ ከቤላ፣ ጀሚል ያዕቆብ፣ ሳሙኤል ዮሐንስ፣ ፍፁም ፍትሕአለው እና ሮኆቦት ሶላሎ ለኢትዮጵያ ዋናው ብሔራዊ ቡድን ለመጀመሪያ ጊዜ ጥሪ የቀረበላቸው ተጫዋቾች ናቸው።

በዛሬው ልምምድ ላይ አዲስ ግደይ ጉዳት አጋጥሞት ልምምድ ያቋረጠ ሲሆን ከህክምና ሪፖርት በኋላ ቀጣይ ሁኔታው እንደሚገለጽ አመልክቷል።

ኢትዮጵያ ከማላዊ ጋር የወዳጅነት ጨዋታዎቿን ግንቦት 29 እና ሰኔ 2 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም