የምርጫ ሂደቱና የድምጽ አሰጣጡ ጥሩ የዴሞክራሲ ምህዳር የታየበት ነው - ኢዜአ አማርኛ
የምርጫ ሂደቱና የድምጽ አሰጣጡ ጥሩ የዴሞክራሲ ምህዳር የታየበት ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ የምርጫ ሂደቱና የድምጽ አሰጣጡ ጥሩ የዴሞክራሲ ምህዳር የታየበት መሆኑን የአማራ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ።
የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሰቢና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይል ንቅናቄ (አዴኃን) ሊቀመንበር ተስፋሁን ዓለምነህ በዛሬው እለት የተካሄደውን የድምፅ አሰጣጥ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም በድምፅ አሰጣጡ በተለይም የህዝቡ ተሳትፎና ድምፁን ለመስጠት ያለው ጉጉት አስደናቂ መሆኑን ተናግረዋል።
የምርጫ ሂደቱ የዜጎች ተሳትፎ እያደገ እና የዳበረ የዴሞክራሲ ስርአት መሰረት እየያዘ መምጣቱን በተግባር ያረጋገጠ ስለመሆኑ አንስተዋል።
በመሆኑም አጠቃላይ የምርጫ ሂደቱና የድምጽ አሰጣጡ ጥሩ የዴሞክራሲ ምህዳር የታየበት መሆኑን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል በዘንድሮው ምርጫ 23 የፖለቲካ ፓርቲዎች ለውድድሩ መቅረባቸውን አንስተው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ በሆነ መልኩ ሂደቱ እስካሁን መቀጠሉ ለዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ያላቸውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ነው ብለዋል።