ቀጥታ፡

በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በምሽት ድምፅ እየሰጡ ይገኛል

አዲስ አበባ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ሰዓት ማራዘሙን ተከትሎ በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች መራጮች በምሽትም ድምፅ እየሰጡ ይገኛል።

ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ ውሎ አሁንም ረጃጅም ሰልፍ ባለባቸው ምርጫ ጣቢያዎች ቀጥሎ እየተካሄደ ነው።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድም የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ ዕኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን አስታውቋል።

በዚህም በአዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ምርጫ ክልል 19 እና 20  ምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተሰለፉ መራጭ ዜጎች ድምፃቸውን እየሰጡ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም