ቀጥታ፡

ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ እኩለ ለሊት 6፡00 ሰዓት ተራዘመ

አዲስ አበባ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ እኩለ ለሊት 6፡00 ሰዓት መራዘሙን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት ላይ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

ቦርዱ በሥምሪት ላይ ያለው የክትትል ቡድኑ ያቀረበለትን ሪፖርት መነሻ በማድረግ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በዚህም መሠረት በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ሥነ-ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49(4) በተደነገገው መሠረት፤ የምርጫው ነፃና ፍትሐዊነት ይበልጥ ያሰፍናል ተብሎ በመታመኑ የድምፅ መስጫ ሂደት ባልተጠናቀቀባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ላይ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ እኩለ ለሊት 6:00 ሰዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

በተጨማሪም የተመዘገቡ መራጮች መርጠው በተጠናቀቁባቸው ጣቢያዎች ላይ አስፈጻሚዎች የድምፅ ቆጠራ ሂደቱን እንዲያከናውኑ ቦርዱ አስታውሷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም