ይበጀናል ላልነው ፓርቲ ድምጻችንን ሰጥተናል - ኢዜአ አማርኛ
ይበጀናል ላልነው ፓርቲ ድምጻችንን ሰጥተናል
አዲስ አበባ፤ግንቦት 24/2018 (ኢዜአ)፦በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ይበጀናል ላሉት ፓርቲ ድምጻቸውን መስጠታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል።
ኢዜአ በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወፍጮ ቤት ምርጫ ጣቢያ ሁለት ያገኛቸው አቶ አለማየው ታምሩ እንደገለጹት፤ የምርጫው ሂደት ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ነው።
በዚህም ድምጻቸውን ላመኑበት አካል መስጠታቸውን ጠቅሰዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ አወቀ እና አቶ ሰለሞን ነጋሽ በበኩላቸው፤ ይበጃል ላሉት ፓርቲ በነጻነት ድምጻቸውን መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሼድ ምርጫ ጣቢያ ቀጠና 4/5 ሲመርጡ ያገኘናቸው አቶ ታደሰ ጌታቸው እና ወይዘሮ ጥሩወርቅ ፍቅረዮሐንስ በበኩላቸው፤ ይመራናል፣ ወደፊት ያስተዳድረናል ብለው ላመኑበት ፓርቲ ድምጽ መስጠታቸውን ተናግረዋል።