ቀጥታ፡

ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ይቀጥላል -የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም. ከማለዳ 12:00 ሰዓት ጀምሮ የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ የማስፈጸም ሂደት በማስፈጸም ላይ መሆኑ ይታወቃል።

ቦርዱ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እስከ 12:00 ሰዓት ሠልፍ ላይ የነበረው ድምፅ ሰጪ ድምፅ ሰጥቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ ድምፅ የመስጠት ሂደቱ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 49 (4) መሠረት ቦርዱ በልዩ ሁኔታ የድምፅ መስጫ ሰዓት ሊያራዝም እንደሚችል ይደነግጋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም