ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ መሆኑን ተመልክተናል - ኢዜአ አማርኛ
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ መሆኑን ተመልክተናል
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሐዊ መሆኑን መመልከታቸውን የኢዜማ ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ገለጹ።
ዛሬ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ሰባተኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በመላ አገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።
54 ሚሊየን 57 ሺህ 861 የምርጫ ካርድ የወሰዱ መራጮች ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማል ብለው ያመኑበትን አካል እየመረጡ ይገኛል።
በምርጫው ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
በየካ ክፍለ ከተማ ምርጫ ክልል 16 ሸማቾች 06/07 ምርጫ ጣቢያ የተገኙት የኢዜማ ፓርቲ የአደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ዳዊት ለገሰ ምርጫው ነጻ፣ ገለልተኛና ፍትሃዊ መሆኑን ተመልክተናል ብለዋል።
የድምፅ አሰጣጡ የተጀመረው ታዛቢዎች በተገኙበት የድምፅ መስጫ ኮሮጆዎች እና ሌሎች የቅድመ ድምፅ አሰጣጥ መስፈርቶች መሟላታቸው ተረጋግጦ መሆኑን ገልጸዋል።
በምርጫ ጣቢያው ህዝቡ ከለሊቱ 10 ሰዓት ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ እየመረጠ መሆኑን ታዝበናል ብለዋል።
በምርጫው ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ አዛውንቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ ነው።
ወጣት ትንሳኤ ስጋቱ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ቀደም ሲል ከነበሩት ምርጫዎች በተሻለ ሁኔታ አካል ጉዳተኞችን ያሳተፈና ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው ብላለች።
ምርጫ ጣቢያዎችን ምቹና ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ተጨባጭ ለውጥ መገኘቱን ተናግራለች።