በክልሉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታ በማዕከላዊ መቆጣጠሪያ ክፍል ክትትል እየተደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታ በማዕከላዊ መቆጣጠሪያ ክፍል ክትትል እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 24/2018(ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የጸጥታ ሁኔታን በተደራጀ መንገድ በማዕከላዊ መቆጣጠሪያ ክፍል ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
የአማራ ክልል ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ማኔጅመንትና የሚመለከታቸው አመራሮች የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የፓትሮል እና የደኅንነት ሁኔታ በቀጥታ እየተከታተሉ ነው።
ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ (ዶ/ር) እና የዋና ጠቅላይ መምሪያው ከፍተኛ ማኔጅመንት አባላት በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለውን የ7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ የሰላም እና የደኅንነት ሁኔታ ከቁጥጥር ክፍል (Command Room) ሆነው በቀጥታ እየተከታተሉ ይገኛሉ።
በዚህም በሁሉም አካባቢዎች የምርጫው ሂደት በሰላማዊ እና በተረጋጋ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል።
የምርጫው ሂደት ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ጀግናው የሀገር መከላከለያ ሰራዊት፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የደህንነት ተቋማትና የክልሉ አድማ መከላከል እና የመደበኛ ፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም የክልሉ የጸጥታ ኃይል ማናቸውንም የጸጥታ ስጋቶች አስቀድሞ ለመከላከል ቁጥጥሩንና ፈጣን ምላሽ የመስጠት ስራውን አጠናክሮ ማስቀጠሉ ታውቋል።